Back To Resource Library
የሥርዓተ ጾታ እና ወጣቶች አተያዮች ለማካተትእና ትግበራ: በማስረጃ ላይ የተመሠረተ የድርጊት መመሪያ
እ.ኤ.አ. በ2022 GAYA የአፈፃፀም አጋሮች ሥርዓተ ጾታ እና ወጣቶችን በስራቸው ውስጥ ማካተትን አስመልክቶ ያላቸውን ዕውቀት፣ አመለካከት እና አሰራሮችን በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት የሚያስችል ሒደታዊ ጥናት አካሂዷል። ይህ የመመሪያ ማስታወሻ ውጤታማ የሥርዓተ ጾታ እና ወጣቶች ማካተትንለማረጋገጥ ለትግበራ አጋሮች ዋና ምክረ ሀሳቦች ለይቶ አስቀምጧል። GAYA ለእያንዳንዱ ምክረ ሐሳብ በዳሰሳ ጥናት ውሂብ አማካኝነት አተያዮችን፣ እነዚህን ምክረ ሐሳቦች ለማቀናጀት የሚረዱ እርምጃዎችን እና የእነዚህን እርምጃዎች አፈፃፀም ለመደገፍ የሚያስችሉ ግብአቶችን ያቀርባል።
በሚመርጡት ቋንቋ (እንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ስፓኒሽ፣ አረብኛ፣ ቤንጋሊኛ፣ ኦሮሞ እና አማርኛ) ስለ GAYA በተጨባጭ-ማስረጃ ላይ የተመሠረቱ ምክረ ሀሳቦች የበለጠ ለማወቅ ከታች ያንብቡ።